Sunday, 30 June 2019

የኦሮሚያ አለም አቀፍ ባንክ ማስታወቂያ ክፍተት


                       

             በሀገራችን  ኢትዮጵያ በአሁኑ ሠአት  ዘርፈ ብዙ የማስታወቂያ አይነቶች እየተስፋፉ ይገኛሉ።ከነዚህም ውስጥ በትላልቅና በትናንሽ የአገልግሎት ተቋማት ፊት ለፊት ላይ  የሚለጠፉ ናቸው።እነዚህም  ተለጥፈው ብዙ ጊዜ ሊቆዩና ላይቆዪም ይችላሉ።
     
         
 በቀጣይም  የምናየው በአንድ ትልቅ የአገልግሎት ሰጭ ተቋም  ላይ ያየሁትን የማስታወቂያ  ስህተትና  እንዲሁም መስተካከል ያለበትን ነገር ነው። ማስታወቂያውም  የኦሮሚያ  አለም  አቀፍ ባንክ ነው።ክፍተቱን ለመረዳት   የማስታወቂያውን ምስል ከታች ይመልከቱ።
             

ስለዚህ  ማስታወቂያዉን  በደንብ ስንመለከተው  እሚስተካከል  ስህተት አለው።ምክንያቱም  በትግርኛ ቋንቋ  ላይ  ኢንተርናሽናል ተብሎ አይፃፍም። በመቀጠልም "ኢንተርናሽናል" የሚለው ቃል እንግሊዝኛ  እንጅ  አማርኛም ሆነ  ትግርኛ ቃል አይደለም።የሀገር ውጭ  ቋንቋ መጨረሻ መምጣት እያለበት  መካከል ላይ ይገኛል። በተጨማሪ ደግሞ  ሁሉም ቋንቋ  ላይ  ኢንተርናሽናል  ይላል  ምኑን ከምኑ መለየት ይቻላል?
     

         የዚህን  ማስታወቂያ ስህተት በመረዳት  ወደ  ትክክለኛው  የማስታወቂያ አፃፃፍ ስርአት ማስኬድ ይቻላል።መፍትሔውም:-  በትግርኛ ኢንተርናሽናል የሚለውን  በመተው  ዓለምለኸዊ በሚለው  ማስተካከል እንዲሁም  አማርኛው ላይ  "አለም አቀፍ " በሚለው ይስተካከል። በይበልጥም በሚከተለው  ቢስተካከል  መልካም ነው።
     
         ባንኪ  ዓለምለኸዊ  ኦሮሚያ   .
ኦሮሚያ  አለም አቀፍ  ባንክ  .
       OROMIA  INTERNATIONAL  BANK  S.C

                        ለመረጃነት ምስሉን  ይመልከቱ።


                              
  
       



       


የማስታወቂያው ስም ምን ይሆን???


     

  ማስታወቂያን በብዙ መንገዶች ልንገልጸው የም ንችል ሲሆን ይህም ሲባል መልዕክቱን ሠዎች በሚረዱልን መልኩ ከተረዱም በሗላ ወደ ውስጣቸው አስገብተው የምናስተዋውቀውን ነገር እነዲገዙ ማድረግ መቻል ነው። ነገር ግን ማስታወቂያው በሠሌዳ ከሆነ  ሲለጠፍም ሆነ ከተለጠፈ በሗላ እንዳይ ቀዳደድ መጠበቅ አለብን።
            
     
          ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ  እንዲያውም  ስልጣኔ በበዛበት  ዘመን  የማስታወቂያ አሠራርናአስተላለፍ ዘዴዎች በግደለሽነት እየተሞሉ  መጥተዋል።ይህም ሲባል ማስታወቂያዎችን ባልሆኑ ቦታዎች  ላይ  በመለጠፍ እንዲቦጫጨቁና ፍፁም ገፅታቸው ጠፍቶ አንባቢያንን  ግራ አሰከማጋባት  ድረስ ደርሠዋል። እኔም  በተረዳሁት መልኩ  በአንድ መንገድ ዳር ላይ  ተለጥፎ ያየሁትን የማስታወቂያ ሠሌዳ ለመገምገም እሞክራለሁ።
            
      
        ማስታወቂያውም  አንዲህ  ይላል እንኳን ደህና መጡ  welcome   እዚህ ላይ  ቀድሞ የሀገር ውስጥ  ቋንቋ መገኘቱ ጥሩ ሆኖ እያለ ነገር ግን በጣም በጣም  ይገርማል ምክንያቱም ይህ  የተለጠፈው ሠሌዳ  የማስታወቂያ ሠሌዳ  ነው ለማለት በጣም ይከብዳል።እንኳን ደህና መጣችሁ ተብሎ የተፃፈው  ከታች ምንንም እሚገልፅ ስለሌለ  ማስታወቂያው ወደ ተለጠፈበት ቦታ  ይመስላል።ለማንኛውም  ማስታወቂያዎች አንደዚህ  ተቦጫጭቀው/ተቀደው/  ይዞታቸውንም እስከሚያጡ ድረስ መጠበቅ በጣም ከባድ ነው።
                 
         
              በአጠቃላይ የማስታወቂያው ስህተት  ይህንን  ይመስላል።
ስለዚህ ማስታወቂያው በሚከተለው  ሁኔታ   ቢስተካከል እጅግ መልካም ነው።
ማስታወቂያው የተፃፈበት ሠሌዳ  እንዳየሁት ተቀዷል ስለዚህ መቀየር አለበት።ይህ የማስታወቂያ ሠሌዳ  ከተቀየረ በሗላም ሙሉ መረጃ የያዘ መሆንና በተጨማሪም  ድርጅት ፣አገልግሎት ሠጭ ተቋምም ሊሆን ይችላል  አድራሻና የሚሠጡትንም አገልግሎት በግልፅ ቢቀመጥ እጅግ መልካም ነው።

  








      







Wednesday, 19 June 2019

አንድ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ቤት ማስታወቂያ ግድፈት


           
              በቅድሚያ  ልናቀው  የሚገባ ነገር  ቢኖር  የማስታወቂያን ምንነት ስንረዳ  ትርጓሜው ግዴታ  በምንሠጠው  አገልግሎት ቦታ ፊት  ብቻ የሚለጠፍ አይደለም። ነገርግን  ለተጠቃሚዎች በቀጥታ  ከቤታቸው (ከአካባቢያቸው) እስከ ማድረስ ያለውንም ያጠቃልላል። ከነዚህም ውስጥ ለምሣሌ:- ከቦታ  ወደቦታ  ተንቀሳቃሽ  የሆኑ  የፁሁፍ ሠሌዳ፣በራሪ ወረቀቶች፣መፅሔቶች፣ጋዜጣዎችን በመጠቀም ማስተዋወቅ ይቻላል።
            
               በቀጣይ የምናየው አንድ የእንግሊዝኛ  ቋንቋ ትምህርት ቤት ማስታወቂያ ግድፈት ነው።ማስታወቂያውን ከታች በምስሉ  ላይ አይቶ መረዳት ይቻላል። እነዲህ ይላል  "real way  school of English"
              
                  ወደ ማስታወቂያው  ስህተት ስመጣ   በመጀመሪያ የሀገር ወጭ ቋንቋ  ተፅፏል፣በቀጣይ የሀገር ውስጥ  ቋንቋ ተፅፏል። ስለዚህ ተገለባብጣል  ማለት ነው።  አማርኛ ቃላቶች ላይ የእንግሊዝኛ ቃላትን ተጠቅመዋል።  የትርጉም ለውጥ አለው፣ በተጨማሪ ደግሞ ፁሁፉ ላይ በጣም ብዙ ስህተት  አለው። ለአብነት ያክል እንመልከት :- ኣቅጣጫ፣ ኣስተማሪዎች ፣ኣድራሻችን ፣ሓውልት ፣ኑና  ባጭር  ግዘ እንደፈለጉት  ይናገራሉ። እነዚህ እና ሌሎችም ጋር  በጣም ብዙ  የቃላት ስህተቶች አለበት። ሌላ ደግሞ  ጥራት ያላቸው አስተማሪዎች እሚለው  ላይ   ጥራት እሚባለው " ለእቃ" እንጅ  ለሠው አይደለም።
                     
                     ለዚህ ማስታወቂያ ማስተካከያ ይሆናል ብዬ  የማምነው :- ቅድሚያ የሀገር ውስጥ ቋንቋ ማስቀደም፣ አማር ኛውም እንግሊዝኛውም" ሪል ወይ "እሚለውን  አማርኛው ላይ  መተርጎም አለበት።  እንግሊዝኛ ፁሁፍ ላይ  ሰህተቱ  ብዙም አይደለም። ነገርግን  ለማስተካከል ያክል  "real way  school of  English language"ቢሆን  አማርኛ ላይ  ደግሞ  የእንግሊዝኛ  ቋንቋ ትምህርት  ቤት  መሆን አለበት ባይ ነኝ። ሌላ ደግሞ  ኣስተማሪዎች=አስተማሪዎች ፣ኣድራሻችን=አድራሻችን ፣ሓውልት =ሐውልቲ ፣ ኑና እንግሊዝኛን  ባጭር ግዘ  እንደፈለጉት ይናገራሉ።  = ይምጡና  እንግሊዝኛ ቋንቋን ባጭር ጊዜ  መናገር ይችላሉ።/ይምጡ እንግሊዝኛ ቋንቋን እንደፈለጉ ባጭር ጊዜ  መናገር ይችላሉ።  "ጥራት" ያላቸው ከማለት ብቃት ያላቸው አስተማሪዎች  ተብሎ ቢስተካከል  ጥሩ ነው ።     ስህተቱን ለመረዳት ያክል  ማስታወቂያውን ይመልከቱ ።


                   
             


በማስታወቂያ ላይ ግደለሽነት ለምን አስፈለገ?


       ማስታወቂያ   እጅግ  በጣም  ብዙ  ጠቀሜታዎች  ያሉት  በሀገር ደረጃ ፣በክልል፣ በወረዳ  እንዲሁም በሌሎችም ጭምር  ጥቅሞች የሚያስገኝ ማለት ነው።ይህም ሲባል  አንድን ምርት፣ አገልግሎት፣ እቃም  ሊሆኑ ይችላል የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም  ለደንበኞች  ማቅረብ  ማለት ነው።በአብዝሀኛው ማስታወቂያዎችን  ስንመለከታቸው  ሲተላለፉ   ሁሉንም የመገናኛ  ዘዴዎችን ያማከሉ ናቸው።  ከእነዚህም ወስጥ ቴሌቭዥን ሬድዮ  ፣በራሪ ወረቀቶች የፁሁፍ ሰሌዳ ፣የማስታወቂያ ሰሌዳ ፣በተለያዩ የመኪና መቆሚያ ቦታዎች ላይ ፣በመብራት ግንዶች እንዲሁም በድርጅቶች በር ላይ የተለጠፉ ናቸው።
                 
       ይህም በሚሆንበት  ጊዜ  ማስታወቂያ ሲሠራ  መቼም ሰሪው ወይም  ማስታወቂያ እንዲሠራለት የሚፈልገው  ሠው እንደት መስራት  እንዳለባቸው  ያውቃሉብየ አምናለሁ።ነገር  ነገር ግን እሚስተዋወቀው ምርት ወይም አገልግሎት  ምን ያክል ለተጠቃሚዎች አመርቂ ነው እሚለው  ላይ  ትኩረት አለመስጠታቸው ነው ።በሌላ መንገድ ደግሞ  ውጭ ላይ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች ላይ በጣም ብዙ  ግደለሽነት አለ  ምሣሌ:- ትኩረት አለመስጠት፣  አዳዲስ መንገዶችን አለመጠቀም ፣ደንበኞች እሚያወዛግብ የማስታወቂያ አይነት በመጠቀም ነው።
                  
      ብዙ ጊዜ ውጭ በሚለጠፉ   ፣በጋዜጣ፣ በመፅሔት በቴሌቭዥን  ማስታወቂዎች  ላይ   በጣም ብዙ ችግር ይታይባቸዋል።እያንዳንዱ  ስንመለከት  ጥራት የሌለው፣ የአካባቢን ገፅ የሚያበላሹ ማለትም የተቀደዱ(የተቦጫጨቁ) ፣አድሬስ የሌለው በጥቅሉ በጣም ብዙ  ስህቶችን እናገኛለን። ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ እቃው የሌለውን ጥራት በማጋነን የሚሰጠው ጥቅምናማስታወቂያ በጭራሽ  እማይገናኙ ናቸው።
በሌላ መልኩ  ደግሞ  አማርኛ  ማስታወቂያ ለመስራት ብዙ ጊዜ የእንግሊዝኛ ቃላቶችን   በመጠቀም  ደንበኞችን እያወዛገቡ ይታያሉ።
                  
     መፍትሔ ሊሆን የሚችለው  ግደለሽነትን   በማስወገድ ማስታወቂያ ሲሠራ  አዳዲስ ፈጠራዎችን  መጠቀም ደንበኞችን ባማከለ ፣ጥንቃቄ በተሞላበት ቢሠራጥሩ ነው። የአካባቢ ገፅታ የሚያበላሹትን ማስወገድ(መቀየር) መቻል አለባቸው። ከዚያም በተጨማሪም ማስታወቂያው  አድራሻ ሊኖረው ይገባል። በቪድዎ  ከሆነ ጥራት ሊኖረው ይገባል። በፅህፈት ከሆነ ስርአቱን ያልጠበቀና የተንዛዛም   መሆን  የለበትም።