Wednesday, 19 June 2019

ሁለት ማ ስታወቂያ በአንድ የአገልግሎት ቦታ ለምን??






        ማስታወቂያ ማለት ለአንድ ነገር መግለጫ ሊሆን የሚችል ስለሚሰጠው አገልግሎት  ግልፅ በሆነ መልኩ ለአንባቢያን(ለደንበኞች) ሣቢና ማራኪ በሆነ መልኩ ማስቀመጥ ነው አላማው። ነገር ግን ዝም ብሎ በግደለሽነት ያለምንም ተነሳሽነት በዘፈቀድ ሊዘጋጅ የሚችል ከሆነ አዋጭነት የለውም።

ከዚህ በመቀጠልም የምናዬው የተለያዩ ቦተዎች ላይ የምናገኛቸው ዘርፈ ብዙ የማስታወቂያ አይነቶችን ስህተት ነው።ይህንንም ስንመለከት  በአንድ ፈርኒቸር መስሪያ ቤት ላይ ተለጥፎ ያየሁትን  ማስታወቂያ ችግር ነው። ማስታወቂያው እንዲህ ይላል ከላይ ኪዳነ ምህረት ፈረኒቸር   ዝቅ ብሎ ደግሞ መዘናግዒ ማዕከል ይላል።
                             "ኪዳነ ምህረት  ፈርኒቸር
                                      " መዘናግዒ ማዕከል"


ያየሁት ማስታወቂያ በአጭሩ ይህን ይመስላል።ይህንን ማስታወቂያ  ማንኛውም ሠው ቢመለከተው  ምንም አይነት ጠንካራ ጎን እንደሌለው ይናገራል። ምክንያቱም  በአንድ የስራ ቦታ ላይ የሚሠጠው አገልግሎት አንድ ሆኖ ነገር ግን ቦታው ላይ የተለጠፈው ማስታወቂያ የሚያሣየው  ሁለት  አገልግሎት እንደሚሠጥ  ከሆነ የሚያመለክተው ዋጋ ቢስነት ነው።  ማስታወቂያውን ስመለከተው ስህተቱ  ሙሉ በሙሉ ነው ብየ አምናለሁ።ምክንያቱም  ማስታወቂያው  አንባቢዎችን(ደንበኞችን) ያወዛግባል፣በመቀጠልም  ለመዝናናት የሚፈልግ ሠው፣እንዲሁም  ፈርኒቸር ለማሠራት  የሚፈልግ  ሠው ቢኖር  ከላይ የተፃፈው  ፈርኒቸር እንደሚሠራበት ፣ከታች ዝቅ ብሎ ደግሞ ""መዘናግዒ ማዕከል"" እንደሆነ ያመለክታል። ባጭሩ ደንበኞችን የመሳብ  ሁኔታ አይታይበትም።በሌላ ሁኔታ ሲታይ  ከላይ ፈርኒቸር እንደሚሰራበት ያመለክታል ውስጥ ላይ ግን እየተሰራበት  ያለው ፑል ማጫወት፣ካራንቡላና ሌሎችም ጭምር ነው።በተጨማሪም ማስታወቂያ  ሀይማኖት ነክ መሆን የለበትም።ለምሣሌ  "ኪዳነ ምህረት "ፈርኒቸር  የሚለው የአገልግሎቱ ስም  ሌላ ሀይማኖት ተከታይ ደንበኞች ላይ  ቅር  ያሠኛል።

   በመጨረሻም ማስታወቂያው  ሙሉ በሙሉ መስተካከል   አለበት።መጀመሪያ ላይ ቤቱ ፈርኒቸር ስራ እየተሠራበት ቆይቶ በሗላ ስራው  ከተቋረጠ የተለጠፈው ማስታወቂያ መነሳት ይኖርበታል።ከዛም በእለቱ ሊሠራ  ተብሎ የታሰበውን አገልገሎቶች ማስታወቂያ  መለጠፍ ይኖርባቸዋል። የፈርኒቸር ስራውን ለመቀጠል ካሰቡ  "መዘናግዒ  ማዕከል" የሚለውን ማስታወቂያ መኖር የለበትም።ከዛም ደግሞ ኪዳነ  ምህረት የሚለው ስም ቢቀየር ጥሩ ነው።ስለዚህ ማስታወቂያው ተለጥፎ ያየሁበት ቤት በአሁኑ ጊዜ እየተሰራበት የሚገኘው "መዘናግዒ ማዕከል" ስለሆነ  ከላይ ያለው ይነሣ ባይነኝ።እንዳዲስም  በጥሩ ሁኔታ " መዘናግዒ ማዕከል" በሚል ቢስተካከል  መልካም ነው።ለመረዳት ያክል ይህን ይመልከቱ።


No comments:

Post a Comment