Monday 1 July 2019

የቃና ፕሮግራም ማስታወቂያ



የkana tv logo ምስል ውጤት



ቃና ቴሌቪዥን  በሀገራችን  ከተጀመረ  አራት  አመታትን አስቆጥሯል።ታድያ  ይህ  ስርጭት  በሃገራችን መጀመሩ ብዙ  የኢትዮጲያ ዜጎች  ለፕሮግራሙ ያላቸው  ፍቅር  ከፍተኛ ነው። ታዳያ ተመልካቾች  ምን  አይነት ጫና እየደረሠባቸው መሆኑንም ማወቅ ተገቢ ነው።

ከላይ ያለውን  ምስል በማየት ለተመልካች  ምን ያክል ጫና አንደሚያደርስ  መገመት አይከብድም።ይህ ምስል እንደምታዩት  "ቃና   ውስጤ  ነው" የሚለው  የቃና ቴሌቭዥን  መፎክር  የብዙዎቸን  ትኩረት  የሳበ  ፅሁፍ  ነው። ይህም  ማለት ብዙ ሰዎች  ለቃና ፕሮግራም  ያላቸው  ፍቅር  በጣም  ውስጣቸውን ሠርስሮ  ሠርፆባቸዋል። ሰዎችም ኧረ  ቃና ፕሮግራም  ወስጤ ነው አንድም ፕሮግራም አንዲያልፈኝ  አልፈልግም እያሉ  ሙሉ ጊዜያቸው  ያጠፍሉ። መስራት እያለባቸው  ሳይሠሩ  ይቀራሉ።

ሌላ ደግሞ  የሚነበቡ መፅሄት፣መፅሀፍት መከታተልና ማንበብ  ትተው  ኧረ እኔ ቃናን ነው መከታተል  እምፈልገው  ቃና እኮ ውስጤ  ነው እያሉ  እሚሸወዱ  ሰዎች  ቁጥራቸው በሃገራችን  እየበዛ መጥቷል። ሌላ ደግሞ  በአለባበስ   ብንመለከት  አብዝሀኛዎቹ  የሀገራችን ሴቶች  ቀሚስ ከመልበስ  ወደ ሱሪ፣ አጫጭር  ቀሚሶች፣ቁምጣ መልበስ የሄዱት  ይህንን  ፕሮግራም በመከታተል ነው። የእኛ  ባህል በተለይም ሴቶች  ቀሚስ  መልበስ እንጅ ሱሪ መልበስ  አይደለም።

ሌላው  በአመጋገብ   ብናይ  እኛ   ኢትዮጲያኖች  በአንድ  ተሰብስበን  በአንድነት መመገብ ነበር ባህላችን   በአሁኑ  ጊዜ  ግን  ሙሉ በሙሉ  ባይጠፋም  ነገር ግን  በመጥፍት  ሂደት ላይ  ነው።  ይህም  የመጣው አሁንም  የውጮችን  ፕሮግራም  በመከታተላችን ነው። በመጨረሻም  ማስተላለፍ  የምፈልገው  ነገር  ቢኖር  ራሳችንን ባህልና  ወግ፣ልማድ በውጮች  ባህል  መቀየር  የለብንም።





No comments:

Post a Comment