Monday 1 July 2019

የሲጋራ ማስታወቂያ


                


       ማስታወቂያ ህብረተሰቡ በምርት  ግብይት ወይም  በአገልግሎት  ረገድ  በሚያደርጋቸው  እንቅስቃሴዎች  ላይ  ተፅዕኖ  በማሳደር  ለሀገሪቱ  ኢኮኖሚያዊና  ፖለቲካዊ  እድገት  ከፍተኛ  ሚና  የሚጫወት በመሆኑ ሀገሪቱ  በገበያ መር  የኢኮኖሚ ስርአት የምትመራ ከመሆኑ አንፃር ገበያው  ጤናማ በሆነ  ውድድር   እንድትመራ በማድረግ  ረገድ ማስታወቂያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ  የሚያደርግ በመሆኑ የማስታወቂያ  አሠራጮች  መብትና ግዴታቸውን በግልፅ  መወሠን በማስፈለጉ   በኢትዮጲያ ህገ መንግስት መሠረት የታወጁ  አዋጆች  አሉ።ቀጥሉም  ያለውን  የማስታወቂያ  ምስል  መተቸት አንችላለን።



        በሀገራችን  የማስተወቂያ  ህግ መሠረት  አንድ ማስታወቂያ  መተዋወቅ  ያለበት  ለህዝቡ  ጥቅም  የሚሠጥ እና   ለሀገር   ኢኮኖሚ  እድገት ይሆናል   ተብሎ  ከታሠበ   ብቻ ነው።  ነገር ግን  ይህንን ማስታወቂያ  ከዚህ  አንፃር  ስናየው  ጥቅም  የሌለው ማስታወቂያ ነው።  ሌላ ደግሞ  በኢትዮጲያ  የማስታወቂያ  ህግ  መሠረት  የሲጋራ  ወይም  የሌሎች አደንዛዥ  ዕፆች  ማስታወቂያዎች የያዘ  ማስታወቂያ  የተከለከለ ነው።
     

ስለዚህ በዚህ ህግ መሠረት  ይህ  ማስታወቂያ  በእኛ ሀገር ሙሉ በሙሉ የተከለከለ እና  አስቀያሚ ማስታወቂያ ነው። ሌላው ደግሞ ይህንን ማስታወቂያ  ከሀገራችን  የማስታወቂያ  ይዘት እና  አቀራረብ  አንፃር  ስናየው  ለምሳሌ  ወንዱ ሴቷ ላይ የሲጋራ  ጭስ በፊቷ ላይ  ሲያለብሳት ይታያል።ይህም ማለት የእርሷን  ስብዕና እየተጋፍት አናያለን። ከዚህ በተጨማሪም  ደግሞ  ሴቷ   በሲጋራ  ሱስ የመያዝ  እድሏ ከፍተኛ  ነው።  በአጠቃላይ ይህ  ማስታወቂያ   በውጮች የአለም ክፍላት  ጥሩ  አስመስለው  ቢያስተዋውቁትም  እንኳ  በእኛ ሀገረ  ግን  የተከለከለና  የተወገዘ ነው።


      በመጨረሻም  የመፍትሔ  ሀሣብ  ሊሆን  የሚችለው   የአደንዛዥ እፅ  ማስታወቂያ  የሚሠሩ  ሠዎችን ማውገዝና  ቅጣት መቀበልም  አለባቸው።  በተጨማሪ  ደግሞ  ምርቱ አንዲጠፋ  ማድረግ  መቻል ነው። ሌላ  ደግሞ ማስታወቂያው በጭራሽ መሠራት የለበትም።   ማህበረሠቡን  ይህ ምርት  ጎጂ  እንደሆነ  ግንዛቤ  ማስጨበጥ   አለብን።


No comments:

Post a Comment