Monday, 1 July 2019

ከዘመን ጋር የዘመኑት የልብስ ማስታወቂያ በኢትዮጲያ



  
      ማስታወቂያ አዳዲስ ነገሮችን ለደንበኞች የት እንደሚገኝ መረጃ ማድረስ ነው፡፡ደንበኞች ደግሞ የሠሙትን ወይም ያዩትን ማስታወቂያ አድራሻ ይዘው ምርቱ ካለበት ቦታ በመሄድ ገዝተው መጠቀም ነው፡፡ነገር ግን ተጠቃሚዎች ይሄ ምርት በታዋቂ ሰዎች መተዋወቁ በጣም አሪፍ ይመስላቸውና ወደ ተግባሩ ገብተው ሲጠቀሙት እናያለን፡፡ ለምሳሌ እንይ ዘመን እየዘመነ ሲሄድ የእኛ የአለባበስ እስታይልም ይዘምናል፡፡

      ይህ ማለት የዘመኑ ፋሽን ልብሶችን መግዛት ፋሽኖች የሚባሉት ደግሞ የምዕራባውያን ባህሎዎች ናቸው፡፡እነዚህን ባህሎዎች እኛ መከተላችን የእኛ ባህል ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ በተግባር እየታየ ነው፡፡ ታድያ እኛ ዘመን እያልን እምናጠፋ ከሆነ "የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች" እንደሚባለው እኛም የራሳችንን ትተን የሠው እንፈልጋለን፡፡ምንም ይሁን ምን ይህ የፋሽን ማስታወቂያ በእኛ ላይ ተፅዕኖ አለበት፡፡ስለዚህ ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡


ታድያ የራሳችንን ባህል ከማጥፋት የእኛን የሆነ ነገር መከተል ተገቢ ይሆናል፡፡ምንአልባት ይሄንን ፋሽን መከተል እንደ ዘመናዊነት ሆኖ ያገለግላል፡፡ለምሳሌ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብናይ ተማሪዎች ለምርቃት የሚገዙት ፋሽን ልብስ ከሀገራቸው አለባበስ ይልቅ የውጭ አለባበስ እስታይለል መልበስ ይፈልጋሉ፡፡ እነሱ ይሄንን አደረጉ ማለት ነገ የእነሱ ልጆች ደግሞ በፍፁም ተመልሳችሁ ባህላችሁን ተከተሉ ቢባሉ ከመመለስ ይልቅ መሳለቂያ ያደርጋል፡፡ስለዚህ አሁኑኑ ከአጉል ፋሽን ተመልሰን የራሳችንን በፋሽን እንደገና ማደስ ለልጆቻችን ማስተማር፣መንገር ባህላችን እንድህ ነበር እያልን ማስገንዘብ አንድ ተገቢ ቁም ነገር ነው፡፡


     ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ታሪካዊ ቦታዎችን፣ቅርሶችን ማስጎብኘት እንድንከባከባቸው ማድረግ የእኛ ሀላፊነት መሆኑን አውቀን ከባህል ያልራቀ ትውልድ አፍሪዎች መሆን አለብን፡፡ በአጠቃላይ ማስተላለፍ የፈለኩት ነገር እነዚህ የፋሽን ልብሶች ምርት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በዚያውም ማስታዎቂያው እየጨመረ ስለመጣ ቢያንስ እንኳን ሙሉ በሙሉ የእኛን አለባበስ ሳንረሳ አንዳንድ ጊዜ ፋሽን መጠቀም ይቻላል፡፡


Advertising of vodka




This advertisement board is found in the city of mekelle, on the road to the airport. It is presenting Ethiopian brand vodka called DESTA VODKA. On the bottom of the board, it states that it was distilled and bottled by DESTA liquors. The first problem I saw with this advertisement was the first thing I saw. 



It was very messed up. With it being iron, it's rusted from being out there through all its conditions for a long while. And also the lacking of proper care for it. The paper that was slapped on it was ripped on some parts and that's how we can tell its rusting. The sign on the left side of the board, right before the writing DESTA, seems to be a lion.




You can't tell when you passing by wither on foot or especially by car. The lion isn't well defined and well drawn. I suppose that's supposed to be the main logo of their company, which should have been more focused on and done greatly. Now the writings were simple and right to the point and the color is very well chosen.




They should clean up the board entirely, giving it a well perceivable image. And the logo of the lion should be redrawn again only this time more defined and to be seen even when just passing by. It is an important part of the sign so it should catch the eye and stay in people's mind to pique the interest in their head about the given product.

Sunday, 30 June 2019

የኦሮሚያ አለም አቀፍ ባንክ ማስታወቂያ ክፍተት


                       

             በሀገራችን  ኢትዮጵያ በአሁኑ ሠአት  ዘርፈ ብዙ የማስታወቂያ አይነቶች እየተስፋፉ ይገኛሉ።ከነዚህም ውስጥ በትላልቅና በትናንሽ የአገልግሎት ተቋማት ፊት ለፊት ላይ  የሚለጠፉ ናቸው።እነዚህም  ተለጥፈው ብዙ ጊዜ ሊቆዩና ላይቆዪም ይችላሉ።
     
         
 በቀጣይም  የምናየው በአንድ ትልቅ የአገልግሎት ሰጭ ተቋም  ላይ ያየሁትን የማስታወቂያ  ስህተትና  እንዲሁም መስተካከል ያለበትን ነገር ነው። ማስታወቂያውም  የኦሮሚያ  አለም  አቀፍ ባንክ ነው።ክፍተቱን ለመረዳት   የማስታወቂያውን ምስል ከታች ይመልከቱ።
             

ስለዚህ  ማስታወቂያዉን  በደንብ ስንመለከተው  እሚስተካከል  ስህተት አለው።ምክንያቱም  በትግርኛ ቋንቋ  ላይ  ኢንተርናሽናል ተብሎ አይፃፍም። በመቀጠልም "ኢንተርናሽናል" የሚለው ቃል እንግሊዝኛ  እንጅ  አማርኛም ሆነ  ትግርኛ ቃል አይደለም።የሀገር ውጭ  ቋንቋ መጨረሻ መምጣት እያለበት  መካከል ላይ ይገኛል። በተጨማሪ ደግሞ  ሁሉም ቋንቋ  ላይ  ኢንተርናሽናል  ይላል  ምኑን ከምኑ መለየት ይቻላል?
     

         የዚህን  ማስታወቂያ ስህተት በመረዳት  ወደ  ትክክለኛው  የማስታወቂያ አፃፃፍ ስርአት ማስኬድ ይቻላል።መፍትሔውም:-  በትግርኛ ኢንተርናሽናል የሚለውን  በመተው  ዓለምለኸዊ በሚለው  ማስተካከል እንዲሁም  አማርኛው ላይ  "አለም አቀፍ " በሚለው ይስተካከል። በይበልጥም በሚከተለው  ቢስተካከል  መልካም ነው።
     
         ባንኪ  ዓለምለኸዊ  ኦሮሚያ   .
ኦሮሚያ  አለም አቀፍ  ባንክ  .
       OROMIA  INTERNATIONAL  BANK  S.C

                        ለመረጃነት ምስሉን  ይመልከቱ።


                              
  
       



       


የማስታወቂያው ስም ምን ይሆን???


     

  ማስታወቂያን በብዙ መንገዶች ልንገልጸው የም ንችል ሲሆን ይህም ሲባል መልዕክቱን ሠዎች በሚረዱልን መልኩ ከተረዱም በሗላ ወደ ውስጣቸው አስገብተው የምናስተዋውቀውን ነገር እነዲገዙ ማድረግ መቻል ነው። ነገር ግን ማስታወቂያው በሠሌዳ ከሆነ  ሲለጠፍም ሆነ ከተለጠፈ በሗላ እንዳይ ቀዳደድ መጠበቅ አለብን።
            
     
          ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ  እንዲያውም  ስልጣኔ በበዛበት  ዘመን  የማስታወቂያ አሠራርናአስተላለፍ ዘዴዎች በግደለሽነት እየተሞሉ  መጥተዋል።ይህም ሲባል ማስታወቂያዎችን ባልሆኑ ቦታዎች  ላይ  በመለጠፍ እንዲቦጫጨቁና ፍፁም ገፅታቸው ጠፍቶ አንባቢያንን  ግራ አሰከማጋባት  ድረስ ደርሠዋል። እኔም  በተረዳሁት መልኩ  በአንድ መንገድ ዳር ላይ  ተለጥፎ ያየሁትን የማስታወቂያ ሠሌዳ ለመገምገም እሞክራለሁ።
            
      
        ማስታወቂያውም  አንዲህ  ይላል እንኳን ደህና መጡ  welcome   እዚህ ላይ  ቀድሞ የሀገር ውስጥ  ቋንቋ መገኘቱ ጥሩ ሆኖ እያለ ነገር ግን በጣም በጣም  ይገርማል ምክንያቱም ይህ  የተለጠፈው ሠሌዳ  የማስታወቂያ ሠሌዳ  ነው ለማለት በጣም ይከብዳል።እንኳን ደህና መጣችሁ ተብሎ የተፃፈው  ከታች ምንንም እሚገልፅ ስለሌለ  ማስታወቂያው ወደ ተለጠፈበት ቦታ  ይመስላል።ለማንኛውም  ማስታወቂያዎች አንደዚህ  ተቦጫጭቀው/ተቀደው/  ይዞታቸውንም እስከሚያጡ ድረስ መጠበቅ በጣም ከባድ ነው።
                 
         
              በአጠቃላይ የማስታወቂያው ስህተት  ይህንን  ይመስላል።
ስለዚህ ማስታወቂያው በሚከተለው  ሁኔታ   ቢስተካከል እጅግ መልካም ነው።
ማስታወቂያው የተፃፈበት ሠሌዳ  እንዳየሁት ተቀዷል ስለዚህ መቀየር አለበት።ይህ የማስታወቂያ ሠሌዳ  ከተቀየረ በሗላም ሙሉ መረጃ የያዘ መሆንና በተጨማሪም  ድርጅት ፣አገልግሎት ሠጭ ተቋምም ሊሆን ይችላል  አድራሻና የሚሠጡትንም አገልግሎት በግልፅ ቢቀመጥ እጅግ መልካም ነው።